Post by ጋዜጠኛ ሰይድ አበራ

የእግር ኳስ ተንታኝና የስፖርት ጋዜጠኛ በብስራት ሬዲዮ 101.1

ክርስቲያኖ ሮናልዶ፡ ከድህነት መንደር እስከ እግር ኳስ ንጉሥነት ያደረሰው ምስጢር ምንድን ነው? ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች! ዛሬ ስለ እግር ኳሱ ዓለም "የማይበገረው ጀግና" ጥቂት ልበል! ከማዴይራ ደሴት የተነሳው ያ ቀጫጫና ምንም ያልነበረው ልጅ፣ ዛሬ በዓለም ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ቀልብ የገዛ፣ የእግር ኳስ ታሪክን የለወጠ ታላቅ ስም ሆኗል። ሮናልዶ ልምምድ ቦታ ቀድሞ ገብቶ ዘግይቶ የሚወጣው ለተሰጥኦው ብቻ ስላልተማመነ ነው። "ችሎታ ያለ ልፋት ምንም ነው" ብሎ ያምናል። ዛሬም በ41 ዓመቱ እንደ 20 ዓመት ወጣት ሜዳ ላይ የሚሮጠው ለራሱ ባለው ጥብቅ ዲሲፕሊን ነው። ሰው ሲተቸው እሱ በሜዳ ላይ በጎል ይመልሳል። ዓለም "አበቃለት" ስትለው እሱ አዲስ ታሪክ ይጽፋል። ውድቀት ለእሱ መሸነፍ ሳይሆን የበለጠ ጠንክሮ ለመነሳት የሚጠቀምበት ድልድይ ነው። አመጋገቡ፣ እንቅልፉና የግል ህይወቱ ሙሉ በሙሉ ለስኬቱ የተገዙ ናቸው። ሰውነቱን እንደ ውድ ማሽን ይንከባከባል። ክርስቲያኖ ሮናልዶ 973 ኦፊሴላዊ ጎሎችን በማስቆጠር የዓለማችን የምንግዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ መሆኑን ያውቁ ነበር? 🐐🏆 ለእናንተ ሮናልዶ ምንድን ነው? የምንግዜውም ምርጥ (GOAT) 🐐 የጥንካሬና የጽናት ምሳሌ 💪 ጎል አነፍናፊው ማሽን 🤖 ከሰሞኑ ግን ፍፁም ሀሰት የሆነ በሱና በሀገሩ ልጆች መካከል ለማቃቃር የታቀደ በሚመስል መልኩ መረጃዎች ሲዘዋወሩ ተመልክቻለሁ። ደግነቱ ኔቬሽ ሮናልዶን አድንቆና ለሱ ያለውን ክብር በመግለፅ አሁን ግን ሮናልናዶ እንደማንኛውም ተጨዋች ነው ማለቱ እንደ ኩነኔ ተቆጥሮ ነበር። ነገር ግን ሙሉ ቪዲዮ ስመለከት አንድምታው እንደዛ አይደለም ሰዎች እንደሚሉት ሳይሆን እንደውም ለጋራ አላማ እዚህ እንዳሉ ወይም እንደቆሙ ነው ሀሳቡ የነበረው።✍️ Ayele A Tesfaye Abate Aragaw Abiy Mikru Afework Eyayu Mohammed Fentaw ጋዜጠኛ ሰይድ አበራ✍️

Post content