Post by Yonas Gorfe

Author, Musician & Producer

ዛሬ እያየነው ያለው ግጭት የሚመራው በፖለቲከኞች ብቻ ሳይሆን በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በቁርዓን እና በታልሙድ ትርጓሜዎችም ጭምር ነው። ፖለቲከኞች ጠረጴዛ ዙሪያ ሲቀመጡ፣ ከኋላቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አማኞች “ይህ የፈጣሪ ፈቃድ ነው” ብለው የሚያምኑትን ከየመጽሐፎቻቸው እየጠቃቀሱ የፖለቲከኞቹን እጅ ይጠመዝዛሉ። በፖለቲካው ዓለም ስምምነትና ድርድር (Compromise) የተለመደ ጉዳይ ነው። በሃይማኖታዊ "መሲሃዊ" ርዕዮተ-ዓለም ውስጥ ግን ድርድር "ክህደት" ነው። ፖለቲካ ሰዎችን በጠረጴዛ ዙሪያ ያቆራኛል፤ ሃይማኖታዊ ጽንፈኝነት ግን ሰዎችን በጦር ሜዳ ያሰልፋል። በፖለቲካ “ተሸነፍኩ” ማለት ሥልጣን መልቀቅ ነው፤ በመሲሃዊ እምነት ውስጥ ግን በድርድር “ተሸነፍኩ” ማለት ፈጣሪንና ትንቢቱን መካድ ማለት ነው። ለዚህ ነው አሁን በመካከለኛው ምስራቅ የምናየው ፍጥጫ ከመሬት፣ ከነዳጅ፣ ከሥልጣን ወይም ከገንዘብ በላይ የሆነው። ይህ ጦርነት በሚሊዮኖች አእምሮ ውስጥ ያለው “ትንቢታዊ ፊልም” ወደ ምድር የወረደበት አሰቃቂ ትዕይንት ነው። https://lnkd.in/dBdYBRjM

Post content