Post by Yimesgen Tarekegn
Emerging Young One Health Champion in Africa | Global Health Security Champion | Pandemic Preparedness | Co-founder | Content Creator | Author
በ1940 ዐ.ም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ 1.2 ሄክታር ስፋት ላይ ሰፈረ - የአሁኑ የአዲስ አበባ ዙ በተለምዶ የአንበሳ ጊቢ ዶ/ር ዮሐንስ ተሰማ ወልደየስ በኢትዮጰያ የዱር እንስሳት ጤና አጠባበቅ የተቋሙ ምክትል ዳሬክተር ሲሆኑ ስለ ተቋሙ አመሰራረት እና አሁን ስላለበት ሁኔታ አጫውቶናል፡፡ የአዲስ አበባ ዙ ወይም የአንበሳ ጊቢ ከመነሻው 7 አንበሶች የነበሩት ሲሆን በጊዜ ሂደት 20 እና ከዛ በላይ አንበሶች፣ አንድ የረዳት የእንስሳት ሀኪም እና በጣም ጥቂት የሚባሉ ሰራተኞች ነበሩት፡፡ በጊዜ ሂደት ቁጥራቸው እየጨመሩ የመጡ የአንበሶች ብዛት በመራባት ምክንያት ከተቋሙ አቅም በላይ ማለትም በቦታ ጥበት ፣ ከባለሙያ እጥረት እና ከሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተገናኘ በያኔው ጊዜ የተወሰኑትን የአንበሳ ግልገሎች ለመቀነስ የተደረገውን ጊዜ ያስታውሳል፡፡ የአዲስ አበባ ዙ ወይንም የአንበሳ ጊቢ ሁለት የእንስሳት ሀኪሞች አስር እና ከዛ በላይ የሚሆኑ ባለሙያዎች ያሉት ሲሆን ጥቂት የማይባሉ አንበሶች ፣ ዝንጀሮ ፣ ጦጣዎች እና ውስን የአዋፍ ዝርያዎች በውስጡ ይገኛሉ፡፡ ተቋሙን ለማሳደግ እና የዱር እንስሳቱንም ለጥበቃ እና የእንክብካቤ ሁኔታ ለማሻሻልና ለማሳደግ በማሰብ በ2004 አመተ ምህረት ላይ ፒኮክ የተሰኘ የዱር እንስሳት ጥበቃ እና እንክብካቤ ማዕከል ለመገንባት በማሰብ በቀድሞ የአዲስ አበባ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ መሰረተ ድንጋዮ የተጣለ ሲሆን የማዕከሉን ግንባታ በየ5 አመቱ በተከታታይ አንዳንድ ደረጃዎችን አጠናቆ ሙሉ በሙሉ በ15 አመት ውስጥ የማዕከሉ ግንባታ ይጠናቀቃል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም አሁን ላይ የLion In Clousure ብቻ መሰራት መቻሉን ለማወቅ ችለናል፡፡ ቦታው ረጅም ጊዜ ያገለገለ እና በበርካቶች ዘንድ የሚታወቅ ከመሆኑ አንፃር ከፍተኛ ድጋፍን እና ትኩረትን ይሻል፡፡ በዘላቂነት የእንስሳቱን ደህንነት ለማስጠበቅ በሚል ተጀምሮ የቀረው የማዕከል ግንባታ እንደሌሎቹ ሁሉ ተገቢውን ትኩረት አግኝቶ እንዲጠናቀቅ የሚመለከታቸው አካላት ሊሰሩበት ይገባል እንላለን፡፡ Wondwossen Gebreyes Andrew Terwin Abiy Ahmed 🇪🇹 Desalegn Gebremedhin Gebreegziabiher Dagmawit Moges Desalegne Mengesha Degefaw Demeke Wondmagegn Mengiste