Post by Yehabke Birhanie

Student at Jimma University

ጌታነህ ወርቁ የኢትዮጵያ ሆቴሎች አባት ነው። ልጁነቱ ተአምራዊ ፣ አስተዳደጉ ከሸዋ ሐረር የተንከራተተ ነው። የትምህርት ፍላጎቱ ፣ የሥራ ትጋቱ ... የአባት ፍቅሩ መለኪያ የለውም ። ሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ልጅነቱን ሊቀማው አንከራቶታል። ለትምህርት ያላንኳኳው በር የለም፤ ሆቴልና ቱሪዝም ግን ከዕድሉ የተጣበቀ የልጅነት ጥሪው ሆነ። የመጀመሪያው በጃንሆይ ስዊዝ ተልኮ ሆቴል አስተዳደርን የተመረቀ ሰው ነው። ንጉሡን በዚያ በእንግድነት ለመቀበል ያደረገው ጉዞ፣ ትምህርቱን የተማረበት መንገድ የትምህርት ተጋድሎ ነው። ወደ ሀገሩ ተመልሶ፦ የራስ ሆቴሎችን ከአዲስ አበባ ወደ ክፍለ ሀገራት አስፋፋ፣ የኢትዮጵያን ሆቴል ለአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ በዘጠኝ ወር ቁሞ አደረሰ። ሂልተንን ከእቅዱ ጀምሮ አስገንብቶ በላሊበላ የመጀመሪያውን የምግብ ትዕይንት (Gastronomy ) አዘጋጅቶ አስመረቀ። በሆንግኮንግ ባለ2000 መኝታውን ሒልተንን መርቶታል ። የኢትዮጵያ ሂልተንን እንዲመራ በኃላፊነት ሲመደብ ሐበሻ ከመራው ድርጅቱ ይከስራል ቀሚል ሹማምንቱ አመጹበት። ኬኒያ ወይም ጃማይካ ሂዶ እንዲመራ ሲጠየቅ ከሀገራ አልወጣም ብሎ ሐራምቤን ወለደ። የሐራምቤ ሆቴል አባት፤ የራስ ባንድ መሥራች ጌታነህ ነው። ድንገተኛው የደርግ እስር ሀገርንም እሱንም የጎዳ መከራ ነበር። በዘመነ ደርግ ኢትዮጵያ የሆቴልና ቱሪዝም ሰው አጥታ መንግሥቱ ኃይለማርያም ሰው ፈልጉልኝ ሲል፤ ካለበደሉ እስር ቤት ለሰባት ዓመት ከአቡነ ጳውሎስ ጋር የተረሳው ጌታነህ ተገኘና ተፈታ። ብዙ ነገር ሊሠራ እያቀደ በጽኑ ታመመ። ወደ ሞት የሚያንደርድር ድካም ሲሠማው ታሪኩን የሙያ ልጁ በገዛለት የወክማን ቴፕ ቀርጾ ዐረፈ። ያ ድምፅ ወደ ጽሑፍ ተቀየረ፣ እውነተኛ መረጃዎች ከያሉበት ታስሰው ቀረቡ፤ የኢትዮጵያ ሆቴሎች አባት የአቶ ጌታነህ ታሪክ በመጽሐፍ ተዘጋጄ። ከማተሚያ ሲወጣ በየቤታችሁ ይገባል። የተወዳጅ ሚዲያ Tewedaje media ባለቤት እዝርሽ Ezra Ejigu የዚህን ወርቃማ ሰው ታሪክ እንዳዘጋጅ እድል ስለሰጠኸኝ አብረን ስለሠራን ከልቤ አመሰግናለሁ ። ክበርልኝ። የጋሽ ጌታነህ ልጅ ሶፊያ ስለብርቱ ትጋትሽ አመሰግናለሁ ። Selamawit Kassa Silesh Girma Gezahegne Abate Gizaw Henoke Seyuome Hagere Ethiopian Hotel Professionals Association -EHPA Ras Hotel Addis Hilton Addis Ababa

Post content