Post by Wabiskills

783 followers

ብዙዎቻችን በየቀኑ የምንጠቀምበት ቴሌግራም (Telegram) ታሪኩ ልክ እንደ አንድ አጓጊ የሆሊውድ ፊልም እንደሆነ ያውቃሉ? ከጀርባው ያለው ታሪክ እጅግ አስደናቂ ነው! የሁለቱ ወንድማማቾች ህልም እ.ኤ.አ በ2013 ፓቭል ዱሮቭ (Pavel Durov) እና ኒኮላይ ዱሮቭ (Nikolai Durov. የተባሉ ሁለት ሩሲያውያን ወንድማማቾች ቴሌግራምን ለአለም አበረከቱ። ፓቭል የገንዘብና የሃሳብ መሪው ሲሆን፣ ኒኮላይ ደግሞ የኮዲንግና የሂሳብ ሊቅ ነበር። ከመንግስት ጋር የተደረገ ፍልሚያ ወንድማማቾቹ ከቴሌግራም በፊት VK የተባለ የሩሲያ ትልቁን የማህበራዊ ሚዲያ መስርተው ነበር። ነገር ግን የሩሲያ መንግስት የተጠቃሚዎችን ምስጢራዊ መረጃ አሳልፋችሁ ስጡን አላቸው። እነሱ ግን ለተጠቃሚዎቻችን ታማኝ ነን፣ አሳልፈን አንሰጥም በማለት ድርጅታቸውን ጥለው፣ ከአገራቸው ተሰደዱ። ፓቭል ከሀገሩ ሲሰደድ ከመንግስት የስለላ ተቋማት ውጪ በምስጢር ከወንድሙ ጋር የሚገናኝበት አስተማማኝ መንገድ ፈለገ። በዚህም የተነሳ ኒኮላይ MTProto የተባለ እጅግ ጠንካራ እና ማንም ሊሰብረው የማይችለውን የዳታ ምስጠራ (Encryption) ቴክኖሎጂ ፈጠረ። ይህ ቴክኖሎጂ የቴሌግራም የላቀ የደህንነት መሰረት ሆነ። ቴሌግራምን ልዩ ያደረጉት 3 ነገሮች፡ የCloud ቴክኖሎጂ፦ መረጃዎችን በስልካችን ላይ ሳይሆን በራሱ ሰርቨር ላይ ስለሚያስቀምጥ ስልካችን ቢጠፋ ወይም ቢቀየር እንኳ ዳታችን በፍፁም አይጠፋም። ያልተገደበ ፍጥነትና መጠን፦ እጅግ ግዙፍ ፋይሎችን (ቪዲዮዎችን እና ዶክመንቶችን) ያለ ምንም ገደብ በሰከንዶች ውስጥ መላክ ያስችላል። ቦቶችና ቻናሎች (Bots & Channels)፦ መረጃን ለላቀ ህዝብ ለማድረስና ስራዎችን በቴክኖሎጂ (Automation) ለማቅለል መንገድ ከፈተ። ባጭሩ ቴሌግራም የተፈጠረው ለተጠቃሚዎች ፍጹም ነጻነትን፣ ምስጢራዊነትን እና ደህንነትን ለመስጠት ነው። ዛሬ ላይ ከመልዕክት መለዋወጫነት አልፎ የቢዝነስ፣ የትምህርት እና የዜና ምንጭ በመሆን የአለማችንን የቴክኖሎጂ መልክ ቀይሯል የዛሬው መረጃ ከተመቻችሁ 👍 ላይክ እና ለጓደኞቻችሁ ሼር ማድረጉን እንዳትረሱ። እንዲሁም በቀጣይ የትኛውን የ technology ባለሙያ ታሪክ በትንሹ እንድንጋብዛቹ ትፈልጋላችሁ ። ሀሳባችሁን በ comment አስቀምጡልን ።👇

Post content