Post by Tsegaye Moges
Psychiatric professional at Hawassa university comprehensive specialized Hospital
ርዕስ፦ የጦርነት ዜናዎችና ጭንቀት (Secondary Trauma) 📺⚠️ በየቀኑ የሚወጡ የጦርነት ዜናዎችን፣ ቪዲዮዎችንና ምስሎችን መመልከት በቀጥታ ባንሳተፍም እንኳ አእምሮአችን ላይ ጭንቀት (Secondary Trauma) ሊፈጥር ይችላል። ራስዎን ለመጠበቅ፦ የዜና ሰዓትዎን ይገድቡ፦ በቀን ውስጥ ለተወሰነ ደቂቃ ብቻ ዜና ይከታተሉ፤ በተለይ ከመተኛትዎ በፊት ስልክ አይመልከቱ። ምንጮችዎን ይምረጡ፦ የተጋነኑና የሚያስደነግጡ መረጃዎችን ከሚያሰራጩ ገጾች ይራቁ። ትኩረትዎን ይቀይሩ፦ የአእምሮ ሰላም የሚሰጡዎትን ስራዎች (ጸሎት፣ ስፖርት፣ ከቤተሰብ ጋር መሆን) ያዘውትሩ። "እርስዎ ወይም የሚወዱት ሰው በጦርነት ምክንያት የስነ-ልቦና ጫና ደርሶባችሁ ከሆነ፣ ኮምፓሽን (Compassion Mental health) ለማገዝ ዝግጁ ነን" ለበለጠ ይቀላቀሉን:: https://lnkd.in/eQVbZai4 https://lnkd.in/eQsGtsst ፀጋዬ ሞገስ (ስነ-አእምሮ ባለሙያ) የአእምሮ ህክምና ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ ለማግኘት ይደውሉ:0956875714 #CompassionMentalHealth #አእምሮጤና