Post by Tirusew Geresu

Communications Consultant | Pan African| Coffee Enthusiast

የግል ትምህርት ቤቶች ትኩረት ካልተደረገባቸው በየአመቱ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ዜጋ እንከስራለን።የግል ትምህርት ቤቶች ሳይረፍድ ይፈተሹ! #privateschools የግል ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎቻቸው የሚመግቡት ጤናማ የሆነ ምግባርን አይደለም።ሀገራዊ ፈተናዎች ጭምር ከፈታኞች ጋር በገንዘብ በመሻረክ ቀድመው ተሰርተው ለተማሪዎች መልስ እስከማደል የሚደርስ ወንጀል በግል ትምህርት ቤቶች ይፈፅማል።ይህም ተማሪዎች ሌብነትን ከትምህርት ቤት በይፋ እንዲማሩት ያደርጋል።የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎች እየከሰርን ነው።በሀገር አቀፍ ደረጃ የወጡ ማስተማርያ መፅሃፍቶች በአብዛኛው የግል ትምህርት ቤቶች ጥቅም ላይ አይውሉም።መምህራን ከወላጅ ገንዘብ የሚቀበሉና corrupt citizen አምራች የሆኑበት ሂደት ይስተዋላል።ከትምህርት ጥራት ጀምሮ እስከ መምህራንና ተማሪዎች ግብረ ገብ ድረስ ሀገር በግል ትምህርት ቤቶች ምክንያት ብዙ ዜጎችን እየከሰረች የምትገኝበት ሁኔታ ለመፈጠሩ ብዙ አመላካቾች አሉ።ትኩረት ካላደረግንበት በየአመቱ ብዙ ዜጎችን እንከስራለን። #abiyahmedali

Post content