Post by Solomon G

MD|Assistant executive at ESPHO|General practitioner at Hayat hospital|Aspire Alumini|previous Chief head of communication officer at EHPSA|Volunteer|Entrepreneur|Afaan oromoo Translator|mental health advocator|

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ! በተለይ ደግሞ በሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ በደክመኝ ሰለቸኝ ባይነት ለምታገለግሉ ኢንተርን እና ረሲደንት ሐኪሞች፤ ይህ መልዕክት የእናንተን የቁም ስቃይና ተጋድሎ በሚገባ አውቃለው * የበዓል ድባብ ለናንተ ትርጉሙ፡ "ዛሬ በዓል ነው እንዴ?" ብላችሁ የምትጠይቁት ሰዓት ሲደርስ ወይም የቲቪ ዜና ስታዩ ብቻ መሆኑን እናውቃለን። የምን TV patient በስልኩ ሲያይ * ጭንቀታችሁ፡ ከቤተሰብ ጋር "እንኳን አደረሳችሁ" መባባል ቀርቶ፤ "የታካሚው ቫይታል (Vital) እንዴት ሆነ?"፣ "ክሮስ ማች (Cross-match) መጣ ወይ?" እና "ያቺኛዋን ኬዝ ፎሎው (Follow) እያደረጋችሁ ነው?" የሚለው ጥያቄ ሰላም አይሰጣችሁም። * የላቦር ዋርድ (Labor Ward) ትግል፡ በዓሉን በበግ ስጋና በደስታ ማሳለፍ ሲገባችሁ፤ ዓይናችሁን ላቦር ዋርድ ላይ ጥላችሁ፣ ጆሯችሁን በፌቶስኮፕ (Fetoscope) አስራችሁ የሕጻናትን የልብ ትርታ ስታዳምጡ መዋላችሁ ትልቅ መስዋዕትነት ነው። > "ለሰው ልጅ ሕይወት ስትሉ የራሳችሁን ደስታ ለሰዋችሁ ሁሉ፤ በዓሉ የሰላምና የጤና ይሁንላችሁ።" የድህረ-በዓል ፕሮግራማችሁ፡ በዓሉን በሥራ ላሳለፋችሁ በሙሉ፣ ከሥራ ስትወጡ የሚጠብቃችሁን ያንን የናፈቃችሁትን የ"እንቅልፍ በዓል" በሰላም ያድርሳችሁ። መልካም በዓል ለእናንተና ለታካሚዎቻችሁ!

Post content