Post by Simretab Esayas
Senior Social Media Reporter || Communication & Public Relation Officer || Writer & Editor || PSIR Graduate
በምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ " ተመራቂ ተማሪዎች ሥራ ጠባቂ ሳትሆኑ ሥራ ፈጣሪ መሆን ይገባችኋል " የምትለው ማሳሰቢያ ድንቅ ነው የምትለኝ 😂 ለምን ብላችሁ የጠየቃችሁኝ እንደሆነ 1ኛ ነገር ሥራ ፍጠሩ የሚለው ሰውዬ እራሱ ተቀጣሪ ሆኖ ሌሎችን አትቀጠሩ ብሎ መምከሩ። 😁 2ኛው ነገር ደግሞ ዩኒቨርስቲዎች አንድ ቀንም እንኳን ከ Theory & practice በዘለለ ለተማሪዎች ሥራ እንዴት እንደሚፈጠር ሳያስተምሩ ሥራ ፈጣሪ ተመራቂ ተማሪዎችን መጠበቃቸው። 😁 3ኛው ነገር ደግሞ አንድ ሚስኪን ተመራቂ ተማሪ በቤተሰብ እጅ ላይ ሆኖ ያለምንም ካፒታልና መንቀሳቀሻ - ብድር ሳይመቻችለት ምን አይነት ሥራ እንዲፈጥር እንደሚጠበቅ በራሱ ግርም ይለኛል።🤭 ይህንን ስል የቅጥር ሥራን በብቸኝነት እያበረታታው ሳይሆን - የቅጥር ሥራ በራሱ በርካታ ትምህርቶችን የሚያስተምር እና ለሥራ ፈጣሪነት እንደ መሸጋገሪያ መሆን የሚችል መሆኑን ለማስረዳት ነው።🙏 Simretab Esayas