Post by Muluken Yewondwossen Kifle
editor
ለውጭ ምንዛሬ ግብይቱ መሻሻል እንዲሁም በጥቅሉ የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል ብሄራዊ ባንክ የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰዱን ቀጥሏል፡፡ ከነዚህ መካከል ደግሞ የህግ/መመሪያ ማሻሻያዎች ይገኙበታል፡፡ ለምሳሌ ባሳለፍነው ሳምንት ባንኩ ከውጭ ምንዛሬ ግብይት እና የትይዩ ገበያን ልዩነት ከማጥበብ አንፃር ያግዛሉ የተባሉ የውጭ ምንዛሬ አሻሻጥ እንዲሁም የፍራንኮ ቫሉታ ህጎችን ለውጥ አድርጎ ወደ ስራ አስገብቷል፡፡ ለውጡ በተለይ ከውጭ ምንዛሬ የዱቤ አጠቃቀም/differed payment/ጋር የተያያዘው እጅግ ወሳኝ እና ስር ነቀል እርምጃ መሆኑ በባንክ ባለሞያዎች ተወስቷል፡፡ እንዲያም ሆኖ ግን የዘርፉ ባለሞያዎች ከአቅም እና ከመሰል አዳዲስ ህጎች ትግበራ እና እውቀት ጋር በተያያዘ ብሄራዊ ባንክ ለባንኮች የለውጥ እና የሞያ ስልጠና ማበጀት እንዲችሉ ተነሳሽነቱ ተጠይቋል፡፡ ስጋት መኖሩም እየተጠቀሰ ነው፡፡ 👉ስጋቶቹ ምንድናቸው? 👉ለውጦቹ ምንድናቸው? 👉ከባንኮችስ ምን ይጠበቃል? 👉ብሄራዊ ባንክ እነዚህን ለውጦች ለምን አደረገ? 👉የብህራዊ ባንኩ ሃላፊ ምን አስተያየት አላቸው? ይህን ዘገባ ሳዘጋጅ:- የኢብባ ዋና ኢኮኖሚስት እና ምክትል ገዥ ፍቃዱ ድጋፌ (Fikadu Digafe, Vice Governor & Chief Economist) ለሰጡት ምላሽ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው፤ ሁላችንም ላገር ነው የምንሰራው እና ይልመድብዎ! በተመሳሳይ፡- 👉ጉምቱው የባንክ እና ኢኮኖሚ ባለሞያ እሸቱ ፋንታዬ Eshetu F. Tessema 👉የአዲስ ቻምበር ምክትል ፀሀፊ እና የኢኮኖሚ ባለሞያ ካሳሁን ማሞ Kassahun Mamo 👉የIMF Ethiopia Mission Head Alvaro Piris ለሰጣችሁኝ ሞያዊ ማብራሪያ አመሰግናለው፡፡ እንዲሁም ስማችሁ እንዲጠቀስ ያልፈለጋችሁ በስራ ላይ የምትገኙ የባንክ ሃላፊዎች እና ባለሞያዎች ለተለመደ ትብብራችሁ ምስጋናዬ ይድረስ:: #NBE_directive #FXD/05/2026 #franco_valuta #Fikadu_Digafe #Vice_Governor #Chief_Economist #Kassahun_Mamo #Eshetu_Fantaye #Alvaro_Piris #IMF_Ethiopia_Mission ለዜናው https://lnkd.in/eEJzrQGk