Post by Mekdela Amba University
811 followers
በሰብል ልማት (Agronomy) እና በዕፅዋት ዝርያ ማሻሻል (Plant breeding) የ2ኛ ድግሪ ፕሮግራሞችን ለመክፈት የውስጥ ስርዓተ ትምህርት ግምገማ ተካሄደ ። ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ግንቦት 29/2018 ዓ ም -ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት የመቅላአምባ ዩኒቨርሲቲ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ በዕፅዋት ሳይንስ ትምህርት ክፍል በሰብል ልማት (Agronomy) እና በዕፅዋት ዝርያ ማሻሻል (Plant breeding) የ2ኛ ድግሪ ፕሮግራምች ለመክፈት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎን በማካተት የዳሠሣ ጥናት ከተደረገ በኋላ ስርዓተ ትምህርት ሲዘጋጅ ቆይቶ ዛሬ ግንቦት 29/9/2018 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ፣ዳይሬክተሮች፣ዲኖች፤ የትምህርት ክፍል ሃላፊዎችና እንድሁም ሁሉም የዶክትሬት ድግሪ ተመራማሪ የስታፍ አባላት በተገኙበት የውስጥ የስርዓተ ትምህርት ግምገማ ተደርጓል። በግምገማው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ዲን አማረ ግርማ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) እንደተናገሩት እነዚህን ፕሮግራሞች መክፈት ያስፈለገበት ዋና አላማ ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ መሠረት በመሆኑ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እንዲሁም ከህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የምግብ ፍላጎት መጨመር ለማመጣጠን በጥራት የሠለጠነና በምርምር ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን የሚያፈልቅ ብቁ ዜጋ ማፍራት አስፈላጊ በመሆኑ እንደሆነ ገልፀልዋል። በዚህም መሠረት ዩኒቨርሲቲው የተመሠረተበት አካባቢ እነኝህን ሙያዎች የሚፈልግ በመሆኑ ለፕሮግራሞቹ ቅድሚያ ተሰጥቶ እንድከፈቱ መደረጉን በመጥቀስ ባለድርሻ አካላትና የዘረፉ ምሁራን አስተያዬት እንድሰጡና ንቁ ተሳትፎ እንድያደርጉ ጋብዘዋል። የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ካሳ ሻውል(ዶ/ር) በበኩላቸው ወርክ ሾፑን በይፋ በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የትኩረት መስክ አንዱ በሆነው በግብርና ዘርፍ አዳዲስ የ 2ኛ ድግሪ መክፈትና ሙያተኞችን ማፍራት ዋናው ተልዕኳችን ነው ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ አክለውም የትምህርት ተደራሽነትን በማስፋት የአካባቢውን ማህበረሰብ መጥቀም የተቋሙ ዋና ተልዕኮ መሆኑን በመግለፅ ፕሮግራም መክፈት ብቻ ሳይሆን ለተጠቃሚዎች በየትኛውም አማራጭ ተደራሽ ለማድረግ መስራት እንደሚጠይቅ አመላክተዋል። የሰብል ልማት (Agronomy) ፕሮግራሙን ስርዓተ ትምህርት ተባባሪ ፕሮፌሰር አማረ ግርማ አቅርበው ያስገመገሙ ሲሆን የዕፅዋት ዝርያ ማሻሻሉን (Plant breeding) ደግሞ አገኝ ሺበሺ (ዶ/ር) አቅርበው አስገምግመዋል። በግምገማው ላይ የተሣተፉ ምሁራን መጨመር አለባቸው እንዲሁም ማስተካከያ ያስፈልጋል ያሏቸውን አስተያዬት በመስጠት መግባባት ላይ ተደርሶበታል። በመጨረሻ የአካዳሚ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር መምህር ደጉ አባተ ከሃገሪቱ የከፍተኛ ትምህር ፕሮግራሞች መተዳደሪያ መመሪያዎች አንፃር ማስተካከያ እና ሙያዊ አስተያዬት ሰጥተው የዕለቱ ግምገማ ተጠናቋል። ለወቅታዊ አና ታማኝ መረዎጃች ገጾቻችንን ይከታተሉ! Website: https://mkau.edu.et/ Facebook:https://lnkd.in/geu_ySS8 Twitter:https://lnkd.in/gC-dU-Az LinkedIn:https://lnkd.in/ggCx3Kt9 YouTube:https://lnkd.in/gakMRDpG Telegram:https://lnkd.in/dYc8da4i