Post by Mahlet Amare Tesfaye

Web Development Student at DevVoltz Company

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ! ✨🙏 ባለፈው የገና በዓል የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር መንገሻ አየነ እና ከፍተኛ አመራሮች በግቢው በመገኘት ከተማሪዎች ጋር በዓሉን በቤተሰባዊ ስሜት ማሳለፋቸው ይታወሳል። ያንን በዓል ልዩ ካደረጉት ኩነቶች መካከል አንዱ በባሕርዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (BiT) የተከናወነው ፕሮግራም ነበር። በወቅቱ የBiT የተማሪዎች ሕብረት እንዲሁም የሴቶች ኮሚቴ አባላት በጋራ በመሆን በዓሉን የማስተባበርና የማደራጀት ትልቅ ዕድል አግኝተን ነበር። 🙌 በተለይም በሴቶች ዘርፍ ፕሬዝዳንትነቴ፣ ለበዓሉ ድምቀት የሆነውን የቡና ሥነ-ሥርዓት ከማዘጋጀት ☕️ ጀምሮ በምግብና በተለያዩ ዝግጅቶች ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው ብቸኝነት እንዳይሰማቸውና በዓሉን በቤተሰባዊ ስሜት እንዲያሳልፉ የበኩላችንን ከፍተኛ ጥረት አድርገናል። ያ በገና በዓል የነበረን መነቃቃትና በጋራ የማክበር ባህል፣ ዛሬም ለትንሳኤ በዓል በድምቀት ቀጥሏል! 🕊️ የዘንድሮውን የትንሳኤ በዓልም ልክ እንደ ገና በዓሉ ሁሉ በሥራ ማስተባበርና በታላቅ ደስታ አክብረናል። 🎊🎉 በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ! 🌼🌼 መልካም የትንሳኤ በዓል! 🕯️✨ Girmaw Ashebir Afomia Andualem Yonatan Amare Tesfaye Habtamu A. Tadesse #BahirDarUniversity #BiT #Easter2018 #WomenEmpowerment #StudentLeadership #Fasika #Ethiopia #CommunityService #HolidaySpirit

Post contentPost contentPost contentPost contentPost contentPost contentPost contentPost contentPost contentPost contentPost contentPost contentPost contentPost contentPost contentPost contentPost contentPost contentPost contentPost content