Post by Habtish hope

--

ለተማሪዎች ደመወዝ የምትከፍለው አስገራሚዋ ሀገር! ወጣቶች ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲገቡ ትምህርታቸውን ጥለው እንዳይወጡ እና በትምህርታቸው ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ መንግስት በየወሩ "የተማሪዎች አበል" (Studiebidrag) በሚል ስም ቀጥተኛ የገንዘብ ክፍያ የሚያቀርብላት አንድ አስገራሚ የአውሮፓ ሀገር አለች። ይህች ሀገር ስዊድን ናት። በስዊድን የትምህርት ሥርዓት ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 20 ዓመት የሆኑ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Upper Secondary School) የገቡ ታዳጊዎች በሙሉ ይህ የገንዘብ ድጋፍ ይደረግላቸዋል። ክፍያው የተማሪዎቹን የትራንስፖርት፣ የመጻሕፍት፣ የምግብ እና ሌሎች ከትምህርት ጋር የተያያዙ ወጪዎችን ለመሸፈን ታስቦ የተዘጋጀ ነው። የዚህ ሥርዓት ዋነኛ መለያው ክፍያው የወላጆችን የገቢ መጠን ሳያገናዝብ ለሁሉም ተማሪ እኩል የሚሰጥ መሆኑ ነው። ተማሪው የመጣው ከባለጸጋም ይሁን ከደሃ ቤተሰብ፣ በትምህርት ገበታው ላይ እስካለ ድረስ ክፍያውን የማግኘት መብት አለው። የስዊድን መንግስት በትምህርት ገበታቸው ላይ ለሚገኙ ለእነዚህ ታዳጊዎች በየወሩ 1,250 የስዊድን ክሮና (በግምት ከ120 እስከ 130 የአሜሪካ ዶላር) ይከፍላቸዋል። የስዊድን መንግስት ይህንን የሚያደርገው ማንኛውም ወጣት በገንዘብ እጥረት ምክንያት ትምህርቱን እንዳያቋርጥ ለማድረግ ነው። ነገር ግን ይህ ስጦታ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የሚሰጥ አይደለም። ተማሪዎች ገንዘቡን በየወሩ ለማግኘት መደበኛ ክፍል ውስጥ መገኘታቸውን (Attendance) መጠበቅ አለባቸው። አንድ ተማሪ ያለ በቂ ምክንያት በተደጋጋሚ ከክፍል የሚቀር ከሆነ፣ መንግስት የሚከፍለውን አበል ይቀንሳል፤ አልፎ ተርፎም ሙሉ በሙሉ ሊያቋርጥበት ይችላል። ወጣቶች በትምህርት ቤት በመቆየታቸው ብቻ ከመንግስት ድጋፍ የሚያገኙበት ይህ አሰራር፣ በሀገሪቱ የትምህርት ማቋረጥን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። __ ሀሳብ እንዴት አያችሗት ቤተሰብ

Post contentPost contentPost contentPost content