Post by G News Media
Decode the unseen
የሀገር አስቀጣይ የትውልድ ገመድ የመበጠስ አደጋ! ልዩ ማህበራዊ ትንታኔ | ክፍል ሁለት (G-24 News Media) “ሀገራት በጦርነት ብቻ አይፈርሱም፤ ትውልዳቸው እውቀትን ሲንቅ በዝምታ ይፈርሳሉ።” ዛሬ በዲጂታል ዓለም “ትምህርት አያስፈልግም” የሚል አደገኛ ትረካ እየተስፋፋ ነው። በተለይ በሶሻል ሚዲያ ላይ ያለ ልፋት ሀብት ማግኘት፣ በአቋራጭ መታወቅ እና ያለ ዕውቀት ስኬት ማሳካት እንደሚቻል የሚያሳዩ መልዕክቶች በተለይ በአፍሪካ እና በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ውስጥ አዲስ የአእምሮ ቅኝ ግዛት ሆነው እየተስፋፉ ይገኛሉ። ይህ ጉዳይ ተራ መዝናኛ አይደለም፤ ትውልድን በዝምታ የሚያበላሽ፣ የሀገርን የሰው ኃይል መሠረት የሚበጥስ እና ጥልቅ ማህበራዊ ውድቀት (Social Decay) የሚያመጣ ስውር አደጋ ነው። 1. ዓለም አቀፍ እና አፍሪካዊ ተሞክሮ፣ የዳበሩ ሀገራት እንዲሁም ስልታዊ አቅጣጫ ያላቸው አፍሪካዊ ሀገራት ትምህርት የሀገር ህልውና መሠረት መሆኑን ቀድመው ተረድተዋል። ስለዚህ ወጣቶቻቸው ከትምህርት ስርዓት እንዳይወጡ በፖሊሲ፣ በፋይናንስ እና በመንግስታዊ ድጋፍ ጠንካራ መዋቅር ፈጥረዋል። የአውሮፓ ተሞክሮ – Sweden፣ በSweden 16 እስከ 20 ዓመት ያሉ ተማሪዎች ወደ ሁለተኛ ደረጃ ሲገቡ ትምህርት እንዳይቋረጥባቸው መንግስት Studiebidrag በተባለ ፕሮግራም ወርሃዊ ድጋፍ ይሰጣል። ይህ ትምህርት የወጪ አይደለም፤ የወደፊት ሀገራዊ ኢንቨስትመንት ነው የሚለውን አመለካከት ያሳያል። የአፍሪካ ተሞክሮ–Rwanda ና Botswana Rwanda ከ1994 የዘር ማጥፋት በኋላ “Knowledge-Based Economy” በመገንባት ቴክኖሎጂን እስከ ገጠር ትምህርት ቤቶች አድርሳለች። Botswana ደግሞ ከአልማዝ ገቢዋ ትልቅ ድርሻ ለከፍተኛ ትምህርትና ለክህሎት ልማት በማዋል ዘላቂ የሰው ኃይል ግንባታን መርጣለች። 2. የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ፣ኢትዮጵያ ውስጥ የወጣቶች ሥራ አጥነት፣ የዲጂታል ክህሎት ክፍተት እና የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ጥያቄዎች እየጨመሩ ነው። በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ላይ የ“ትምህርት አያስፈልግም” ትረካ መስፋፋት ችግሩን የበለጠ ያባብሰዋል። በተለይ የዲጂታል ዓለም መስፋፋት እየጨመረ ቢሆንም የቴክኖሎጂ እውቀት በተመጣጣኝ ፍጥነት አልጨመረም። ይህ በቀጣይ የሥራ ገበያ ላይ ከፍተኛ አደጋ ሊፈጥር ይችላል። 3. የማህበራዊ ሳይንስ ትንታኔ፣ አንድ ማህበረሰብ ለሳይንስ፣ ለፈጠራ፣ ለዲሲፕሊን እና ለሥራ ስነ-ምግባር ያለው ክብር ሲደክም የሀገር ህልውና በቀጥታ አደጋ ውስጥ ይገባል። የ“ቀላል ስኬት” ትረካ ወጣቶችን ለዓመታት በትዕግስት፣ በስርዓት እና በተግባር የሚገኘውን እውነተኛ እውቀት እንዲንቁ እያደረገ ነው። ይህ የአእምሮ ጦርነት የማህበረሰቡን የፈጠራ አቅም በማዳከም ሀገርን ወደ ጥገኝነት ይመራል። ችግሩ ትምህርትን መተው አይደለም፤ ትምህርትን ከሕይወት ክህሎትና ከሥራ ገበያ ጋር እንደገና ማገናኘት ነው። 4. የፋይናንስ እውቀት እና የኢኮኖሚ ህልውና፣ በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘመን ትውልዱ መደበኛ ትምህርት ብቻ ሳይሆን የፋይናንስ እውቀት (Financial Literacy) መያዝ አለበት። አሜሪካ የሚጠቀምበት ዶላር በዓለም አቀፍ ገበያ ከፍተኛ ተቀባይነት አለው። የኢትዮጵያ ብር ግን የውጭ ግዢ አቅሙ ውስን ነው። ስለዚህ ምርት ሳይጨምር እና የፋይናንስ እውቀት ሳይሰፋ ኢኮኖሚ ማጠናከር አይቻልም። በዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶች ዘመን ቴክኖሎጂን የማያውቅ ሰው በመሠረታዊ የገንዘብ አጠቃቀም ላይ እንኳ ጥገኛ ይሆናል። 5. ሕጋዊና ስልታዊ እይታ፣ ይህ የፀረ-ትምህርት ቅስቀሳ በቀጥታ አንድን ብሔር ወይም ሃይማኖት ባያጠቃምም በረጅም ጊዜ ሀገርን ስለሚያዳክም በዝምታ ሊታለፍ አይገባም። የትምህርት ተቋማት፣ የፍትህ ተቋማት እና የሚዲያ ተቋማት በመቀናጀት የትምህርትን ዋጋ የሚያሳድጉ አዎንታዊ ይዘቶች መፍጠር አለባቸው። ነፃነት ማለት የሀሳብ ገበያን ማስፋት እንጂ ትውልድን ወደ ድንቁርና መግፋት አይደለም። የ G-24 News ማጠቃለያ፣ ሀገራት በኢኮኖሚ ከመውደቃቸው በፊት በአስተሳሰባቸው ይወድቃሉ። ትውልድ እውቀትን ሲያቃልል፣ ጥናትና ምርምር ዋጋ ሲያጣ እና ማህበረሰቡ ይህንን እያየ በዝምታ ሲያልፍ ሀገር ቀስ ብላ ትወድቃለች። ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ፣ በArtificial Intelligence እና በዲጂታል ዲፕሎማሲ ለመወዳደር የሚያስፈልጋት በዕውቀት የተገነባ፣ በስርዓት የተቀረፀ እና የፈጠራ አቅም ያለው ትውልድ ነው። ኢትዮጵያ ትውልድን ለመጠበቅ የትምህርት፣ የሚዲያ እና የዲጂታል ፖሊሲዎቿን እንደገና ልትፈትሽ ይገባታል። ይህ የፖሊሲ ምርጫ ብቻ ሳይሆን የሀገር ህልውና ጉዳይ ነው። G-24 News Media — ከመረጃ ባሻገር! ለትንታኔው ግብዓት ሁለቱ የምጣኔ ሃብት ተንታኞች ሐሰን ኢንጃሞንና በፍቃዱ ኤባን ፅሁፍ ተጠቅመናል፣ለዚህም የዝግጅት ክፍሉ ያመሰግናል። በመሃመድ ስራጅ ለተጨማሪ ሚዛናዊ፣ በጥናት የተደገፉ እና ተጠያቂነትን የሚያሰፍኑ የአፍሪካ ቀንድ የጂኦፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ ፖሊሲ ትንታኔዎች G-24 NEWS ሚዲያን ይከታተሉ፦ 🌐 ድረ-ገፅ: www.mechal.org.et 📱 ፌስቡክ: fb.com ✈️ ቴሌግራም: t.me/G24newsMedia