Post by Fluse Media

2,499 followers

አቶ ይህንዓለም አቅናው መሸሻ የአማራ ባንክ ፕሬዚዳንት ተደርገው ተመረጡ። የአማራ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ትናንት ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ባደረገው ጥልቅና ስትራቴጂካዊ ስብሰባ፣ አቶ ይህንዓለም አቅናውን አዲሱ የአማራ ባንክ ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል። አዲሱ ፕሬዚዳንት አቶ ይህንዓለም አቅናው በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከ24 ዓመታት በላይ የዘለቀ ስኬታማ የሥራ ልምድ ያላቸው ሲሆን፣ ይህንን ተግባራዊ ተሞክሯቸውን በዓለም አቀፍና በአገር አቀፍ የላቀ የትምህርት ዝግጅትና የሙያ ማረጋገጫዎች ያገነቡ መሪ ናቸው። የአካዳሚክና የሙያ ብቃታቸውን በተመለከተ፦ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ በሂሳብ አያያዝ (BA in Accounting) የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። በቴክኖሎጂና ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ያላቸውን እውቀት ለማሳደግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢንፎርሜሽን ሲስተምስ (BSc in Information Systems) በ2005 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አጠናቀዋል። በለንደን፣ ዩናይትድ ኪንግደም ከሚገኘው ታዋቂው የታወቀላቸውና የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ማህበር (FCCA - ACCA (Association of Chartered Certified Accountants) UK) ተምረው የላቀ የሙያ ማረጋገጫ ማዕረግ በ2013 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ተቀናጅተዋል። እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት የExecutive MBA (የሥራ አመራር ማስተርስ) ዲግሪያቸውን በ2014 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) አግኝተዋል። ​የሥራ ልምድ ዝርዝር (Professional Experience) በተመለከተ፦ አቶ ይህንዓለም አቅናው ከ24 ዓመታት በላይ የዘለቀ የሥራ ዘመናቸውን በኢትዮጵያ ቀዳሚና ግዙፍ የግል ባንክ በሆነው ዳሽን ባንክ ውስጥ ያሳለፉ ሲሆን፣ ከታችኛው የባንክ ኦፕሬሽን ጀምሮ እስከ ከፍተኛው የአመራር እርከን ድረስ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ አገልግለዋል። ለአብነት ያኽል፤ የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ (Branch Manager) በመሆን አገልግለዋል። በተለያዩ የዳሽን ባንክ ቅርንጫፎች ውስጥ በሥራ አስኪያጅነት በመስራት፣ የቅርንጫፍ ኦፕሬሽኖችን መርተዋል፣ የደንበኞችን ቁጥር አሳድገዋል እንዲሁም የተቀማጭ ገንዘብ (Deposit) አሰባሰብን አጠናክረዋል። በዳሽን ባንክ ዋና ቢሮ የክሬዲት ዲፖርትመት (credit department) ዳይሬክተር በመሆን ሰርተዋል። በብድር ክፍል ውስጥ ትልቅ አሻራ አሳርፈዋል። በኋላም የስትራቴጂ መምሪያ ኃላፊ ( Strategy Department Director) በመሆን በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ በኃላፊነት በመምራት የውስጥ አሰራር ሥርዓትን እና ስትራቴጂካዊ አሰራሮችን አዘምነዋል። ትልልቅ ስራዎችን ሰርተዋል። በምክትል ፕሬዚዳንትነት ደረጃ (Vice President) በመሆን ሰርተዋል። በዳሽን ባንክ ከፍተኛ ማኔጅመንት ውስጥ በምክትል ፕሬዚዳንትነት ደረጃ ቁልፍ ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን እና ዘርፎች በዋናነት መርተዋል። የስትራቴጂክ እና ከስተመር ኤክስፔርያስ (Strategy & Customer Experience) ፣ እንዲሁም የባንኩን Retail & SME ዘርፍ በቺፍነት መርተዋል። በዚሁ ቆይታቸው በድስትሪክት ደረጃ በርካታ የባንክ ቅርንጫፎችን በአንድ ላይ በማስተናገድ፣ የስትራቴጂ አፈጻጸምን፣ የሰው ኃይል ልማትንና የቅርንጫፎችን ሁለንተናዊ ዕድገት በበላይነት መርተዋል። ከዚህ ባሻገር በባንኩ ውስጥ በነበራቸው ተሳትፎ ዋና ዋና የአመራር ስኬቶችና ክህሎቶች የተጎናፀፉ እንደሆኑ የግል ማህደራቸው ያሳያል። የባንኩን የዲጂታል ሽግግር ማለትም ባንኩ ወደ ዘመናዊና ቴክኖሎጂ ተኮር አሰራር በሚያደርገው ጉዞ ላይ የላቀ አስተዋጽዖ አበርክተዋል። በሂሳብ አያያዝና በፋይናንስ ኦዲት (FCCA) ያላቸውን ዓለም አቀፍ እውቀት በመጠቀም የባንኩን የውስጥ አሰራር እና ቁጥጥር ሥርዓት አጠናክረዋል። የስትራቴጂካዊ ውሳኔ በመስጠት የባንኩን የረጅም ጊዜ ዕድገት የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎችንና መመሪያዎችን በመቅረጽ ረገድ የዳበረ ልምድ አግኝተዋል። በሁሉም ዘርፍ በአመራርነት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። በአሁኑ ወቅት አማራ ባንክ የሚገኝበትን የዕድገት ምዕራፍና ያለበትን መስቀለኛ መንገድ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ አዲሱ ፕሬዚዳንት ካላቸው የቴክኖሎጂ፣ የስትራቴጂ ፣ የፋይናንስ እና ኦፕሬሽን ማኔጅመንት ጥልቅ እውቀት አንጻር በባንኩ ውስጥ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን፣ የደንበኞችን ፍላጎትና የአገልግሎት ጥራት ተግዳሮቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በመፍታት ባንኩን ወደ ተሻለና አስተማማኝ የዕድገት መስመር ያስገቡታል ተብሎ ትልቅ ተስፋ ተጥሎባቸዋል። ስለ አቶ ይህንዓለም አቅናው ከቅርበ‍ ጓደኞቻቸው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ አቶ ይህንዓለም ባለራዕይ፣ ታማኝ፣ የሙያ ስነምግባሩን የሚያከብር፣ በስትራቴጂካዊ እድገት እና በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ረገድ ተግባራዊ ልምድ ያለው፣ የፋይናንስ አፈጻጸምን በማሻሻል፣ አደጋን በማስተዳደር እና የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት ፈጠራን በማሳደግ የተሻለ አሰራር የሚዘረጋ ብለህ ሰው ነው ብለዋል። አያይዘውም አዲሱ ተሿሚ የአማራ ባንክ አሁን ካለበት መሰረታዊ ችግር ይታደገዋል የሚል የፀና ግምታቸውን አስቀምጠዋል። ምንጭ ;- ዘ-ሀበሻ #finance #business #Ethiopia #banking

Post content