Post by Fikrte Wentela

Psychiatric professional at Community Health Center

#1ድባቴ (depression) ምን አይነት ህመም ነው? ከአዕምሮ ህመም -በአብዛኛው ጊዜ ከሚከሰቱ መካከል ሲሆን አንድ ሰው የስሜት ዝቅታ ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ የባህሪ፡የአስተሳሰብ መለዋወጥ ይከሰታል። •ይህም ህመም መገለጫው ብያንስ ለሁለት ተከታታይ ሳምንታት የሚያሳዩት ምልክቶች አማካኝነት የዕለት ተዕለት ተግባርን እንዳያከናውኑ አሉታዊ ተፅዕኖ ያደርግባቸዋል። •አንድ ሰው በድባቴ ህመም ውስጥ ሲሆን ምን አይነት ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል ብለን ስንመለከት ከታች ከተዘረዘሩት ብያንስ አምስቱን ሊያሳይ ያስፈልጋል። እነሱም -ከፍተኛ ምክንያት የለሽ መከፉትና ማልቀስ -በዕለተ ተዕለት ህይወት ውስጥ ፍላጎት ማጣት፣መዝናናት አለመቻል -ከፍተኛ ብስጭት - የመረበሽ ስሜት -ማህበራዊ መነጠል፣ብቸኝነትን ማብዛት - ከፍተኛ ምክንያት የለሽ የድካም ስሜት፣የጡንቻ መዛል፣ቁርጥማት፣የጀርባ ህመም - በስራ፣በትምህርትና ቤተሰባዊ ሀላፊነቶች ላይ ከተገቢው በላይ መጨነቅ -የእንቅልፍ መቸገር - በራስ የመተማመን ስሜት መቀነስ ፣የጥፋተኛነት ስሜቶች፣ - ዋጋ ቢስና ራስን ዝቅ አድርጉ ማሰብ - ደካማ እና የቀነሰ ትኩረት መኖር - አፍራሽ እና መጥፎ ሀሳቦችን ማሰብ - ራስን የማጥፋት ሀሳብ እና ራስን የመጉዳት ወይም ራስን የማጥፋት ሙከራዎችን ማድረግ የመሳሰሉት የድባቴ ችግርን ያሳያል። እነዚህን ምልክቶች እኛ ላይ ወይም ሌሎች ላይ ስንመለከት የስነ አዕምሮ ባለሞያን በማማከር ህክምናን መከታተል ይኖርብናል።ይህም ህክምና በመዳኒትና በንግግር ህክምና የሚታከም ነው። • ድባቴ ህመም በአሁን ጊዜ ገዳይ ከምንላቸው ህመሞች አንዱ ነው።ይህም ህመም በራሱ ገዳይ ሆኖ ሳይሆን በሰዎች ስሜት ውጥረት ውስጥ በሚፈጠረው ራስን የማጥፋት ሀሳብና ሙከራ አማካኝነት ሲሆን እነዚህ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ስለ ራሳቸው ያላቸው አመለካከት፦ ራሳቸውን እንደማይጠቅሙ ማሰብ -መኖራቸው ትርጉም አልባ እንደሆነ መቁጠር -በሞትኩና በተገላገልኩ የሚሉ ንግግሮችን ሲደጋግሙ እናመለከታለን።ስለዚህ እንደዚህ ለሚሉ ሰዎች ትኩረትና የህክምና ባለሞያ እንድያማክሩ ማድረግ ይኖርብናል። •ህክምናው ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል ብለን ስንጠይቅ ታካሚውና ባለሞያው በጋራ የሚሰሩት ተግባር ነው።ይህም ማለት ለታካሚው ሚሰጡት መድሀኒቶች ምን ያህል ይጠቅመዋል የሚለው ላይ ትኩረት ይሰጠዋል።በዚህም ምክንያት ሰዎች ላይ የሚሰጠው ለውጥ ከሰው ሰው ሊለያይ ይችላል።ስለዚህ ታካሚው የሚሰጠውን ህክምና በአግባቡ መውሰድና መከታተል ይኖርበታል፤እናም ህክምናው በባለሞያው እገዛ ሊቀጥልና እንዲውም መስተካከል ያለባቸው ነገሮች ላይ በመስራት ወደ ተሻለ ለውጥ ማምጣት ትልቁ ስራ ነው። •ያለ ባለሞያ እገዛ ውጭ የሚደረግ የህክምና ክትትል ማቆም ህመሙን ሊያባብስ ይችላል፤ከዚህም የተነሳ ህክምናውን ከባለሞያ ማማከር ውጭ ምንም ነገር ማድረግ አኖርብንም። fikir w(psychiatry professional )

Post content