Post by Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) - ኢሰመኮ

22,591 followers

የሳምንቱ #HRConcept: የሕፃናት ከጉልበት ብዝበዛ የመጠበቅ መብት ... የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 36(1) (መ) ማንኛውም ሕፃን ጉልበቱን ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ፤ በትምህርቱ፣ በጤናውና በደኅንነቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሥራዎችን እንዲሠራ ያለመገደድ ወይም ከመሥራት የመጠበቅ መብት አለው። ዓለም አቀፉ የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 32(2)(ሀ-ሐ) ተዋዋይ ሀገራት በተለይ፡- - ዝቅተኛ የቅጥር ዕድሜን ወይም ዕድሜዎችን ይወስናሉ፤ - የሥራ ሰዓትንና የቅጥር ሁኔታዎችን በተመለከተ ተገቢውን ደንብ ያወጣሉ፤ - ይህ አንቀጽ በሚገባ በሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ ተገቢ ቅጣቶችን ወይም ሌሎች ክልከላዎችን ያስቀምጣሉ። https://ehrc.org/?p=38110 #Ethiopia #KeepWordSafe #ጤናማቃላት በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

Post content

Video Content