Post by Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) - ኢሰመኮ

22,591 followers

የሳምንቱ #HRConcept: በቂ ምግብ የማግኘት መብት ... የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባህላዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 11 (1) እና (2) ማንኛውም ሰው በቂ ምግብ፣ ልብስና መኖሪያ ቤትን ጨምሮ ለራሱና ለቤተሰቡ በቂ የኑሮ ደረጃ የማግኘት መብት አለው። የዚህ ቃል ኪዲን ተዋዋይ ሀገራት ማንኛውም ሰው ሳይራብ ለመኖር ያለውን መሠረታዊ መብት በመገንዘብ በተናጠልም ሆነ በዓለም አቀፍ ትብብር አማካኝነት፦ ቴክኒካዊና ሳይንሳዊ ዕውቀትን በሙሉ በመጠቀም የምግብ አመራረት፣ ክምችትና ስርጭት ዘዴን ለማሻሻል፣ የአልሚ ምግብ መሠረታዊ ዕውቀቶችን ለማሰራጨት፣ ከፍ ያለ ውጤት ያለው የተፈጥሮ ሀብት ልማት እና አጠቃቀም እንዲኖር የግብርና ሥርዓቱን ለማሻሻል፤ ምግብ አስመጪና ላኪ ሀገራት የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ግምት ውስጥ በማስገባት በፍላጎታቸው መሠረት ፍትሐዊ የዓለም የምግብ አቅርቦት ስርጭት እንዲኖር ለማረጋገጥ ዝርዝር መርኃ ግብሮችን ጨምሮ አስፈላጊ እርምጃዎችን ይወስዳሉ። 🔗 https://ehrc.org/?p=37963 #Ethiopia🇪🇹 #KeepWordSafe #ጤናማቃላት በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

Post content

Video Content