Post by Endlessm
1 follower
ቻይና የ«መደመር» መጽሐፍን ወደ ራሷ ቋንቋ እየተረጎመች ነው ተባለ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጻፈው የ«መደመር» መጽሐፍ፣ ኦፊሴላዊ የቻይንኛ ቋንቋ የትርጉም ሥራው ተጠናቆ በቅርቡ ለንባብ ሊበቃ መሆኑ ተሰማ። ይህም ፍልስፍናው ከተወለደበት የኢትዮጵያ ምድር ተሻግሮ አህጉራትንና የተለያዩ ባህሎችን የማስተሳሰር ትልቅ ዓለም አቀፋዊ ተደራሽነትና ተቀባይነት እያገኘ ለመምጣቱ ማረጋገጫ መሆኑን መንግስታዊ ሚዲያ ዘግቧል። እንደ ቻይና ዓይነት የረጅም ዘመን የፖለቲካ ፍልስፍና እና የራሷ የርዕዮተ-ዓለም መስመር ያላት ኃያል አገር «መደመር»ን ወደ ራሷ ቋንቋ መተርጎሟ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊና ፖለቲካዊ አንድምታ አለው። ኢትዮጵያ ባለፉት ዘመናት ከውጭ የሚመጡ እንደ ካፒታሊዝምና ሶሻሊዝም ያሉ ርዕዮተ-ዓለሞችን ስታስተናግድ የኖረችበትን የታሪክ ምዕራፍ በመቀየር፣ አሁን ግን የራሷን አገር በቀል ፍልስፍና ወደ ውጭ የምትልክ ተፅዕኖ ፈጣሪ አገር ለመሆኗ መጽሐፉ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል። መጽሐፉ አፍሪካን፣ መካከለኛው ምስራቅን፣ ደቡብ እስያንና አሁን ደግሞ ምስራቅ እስያን ተደራሽ ማድረጉ የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ አቅም በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድገው ተገልጿል። #Medemer #Ethiopia #China #GlobalDiplomacy #AbiyAhmed #MedemerInChinese #AfricanPhilosophy