Post by Dr. Ephrem Kelemework
Quality and Safety Lead | Empowering Individuals & Organizations | Excellence & Efficiency Strategist | Researcher | Trainer in Leadership, Innovation, Wellbeing & Professional Growth
Universal Science of Problem Solving በቅርቡ እዚህ መንደር ዞር ዞር ስል አንድ ገራሚ አባባል ሳበችኝና ጠቆም አድርጌ ሙሉ ሃሳቧን አነበብኳት፡፡ «የትምህርት ዘሩ አንድ ነው ያም ችግር መፍታት ነው!» ትላለች፣ በዶ/ር Letenah Ejigu Wale የተከተበች ናት፡፡ ሳጤነውና ስመረምረው፣ እውነትም የየትኛውም ትምህርትና የትምህርት ዘርፍ ዓላማው፣ ግቡ፣ ውጤቱ ችግርን መፍታት መሆኑ ምን ያህል እውነት እንደሆነ ይበልጥ ተረዳሁ። ዛሬ የህክምና ትምህርትና ልምምድ በየዕለት ከዕለት ተግባሩ ለመላው የትምህርትና የስራ ዘርፍ ሁሉ፣ ለመላው የቢዝነስና ተቋማዊ አሰራር ሁሉ ችግሮችን መፍታት እንዴት እንደሆነ በደማቁ የሚያስተምርበትን የችግር አፈታት ሂደት በዚህ አጭር ጦማር ከትቤላችኋለሁ፡፡ የሶስት ደቂቃ ንባብ ነች፡፡ መልካም ቆይታ!