Post by Biruk M. Tenaw

Sport Science Researcher | Exercise Psychology & Athletic Performance | Adaptive Physical Activity | Seeking Fully Funded PhD | Youth Sport Development – Ethiopia

#የፈሳሽ_ማሽን_ወይስ_የጂኦሜትሪ_ቀመር? ሉዊስ ኤንሪኬ እግር ኳስን ወደ "Controlled Chaos" (ቁጥጥር ወዳለው ምስቅልቅል) ሲቀይረው እናይ ይሆን ?! የዘንድሮው የ2025/26 የሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ተራ የእግር ኳስ ጨዋታ አይደለም፤ በዘመናዊው እግር ኳስ ውስጥ የታዩ ሁለት ተቃራኒ ፍልስፍናዎች ማስተርፒስ የፊት ለፊት ጦርነት እንጂ! በአንድ በኩል የሚኬል አርቴታ ፍፁም ዲሲፕሊን እና የጂኦሜትሪ ስሌት፣ በሌላ በኩል ደግሞ የሉዊስ ኤንሪኬ ፈሳሽ ማሽን (The Fluid Machine)... ብዙዎች ፒኤስጂ (PSG) ከኮከብ ተጫዋቾች ጥገኝነት ሲወጣ ይዳከማል ብለው ገምተው ነበር። ነገር ግን ኤንሪኬ እያንዳንዱ ተጫዋች እንደ አንድ የተቀናጀ አካል የሚንቀሳቀስበት፣ በመስመሮች መለዋወጥ እና በከፍተኛ የሽግግር ፍጥነት ላይ የተመሰረተ አስፈሪ መዋቅር መገንባት ችሏል። በዚህ ጽሁፍ የፒኤስጂን የታክቲክ ስብራት በስፖርት ሳይንስ እና በላቁ የዳታ ትንተናዎች ደግፌ በዝርዝር ዳስሻለሁ። በዚህ ጽሁፍ በሰፊው የሚነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፡ 1. "ቨርቲካል ቲኪ-ታካ" (Vertical Tiki-Taka)፦ ኤንሪኬ ባህላዊውን የኳስ ቁጥጥር ወደ ፈጣን የመስመር ስብራት እንዴት ቀየረው? 2. የ2-3-5 የማጥቃት ካርታ (The Tactical Map)፦ በአርሰናል ባለ 4 ተከላካይ መስመር ላይ የቁጥር ብልጫ (5v4 Overload) የመፍጠር ስልት። 3. የ3ቱ የአውድማ መሳሪያዎች (The Tactical Triggers)፦ የማያቋርጥ የቦታ መለዋወጥ፣ የ5 ሰከንድ የኳስ ማገገሚያ ጫና (Counter-pressing) እና የInverted Full-backs ሚና። እርስዎስ እንደ አንድ የእግር ኳስ ወዳጅ እና ተመልካች ፣ የኤንሪኬ "ፈሳሽ ማሽን" የአርቴታን ጥንቁቅ የመከላከል ግንብ (Resting Defence) ሰብሮ ማለፍ ይችላል ወይስ የአርሰናል የታክቲክ ትዕግስት ያሸንፋል? 👇 ሙሉውን ጥልቅ ታክቲካዊ ትንተና እና ሳይንሳዊ ዳታ ከታች ባለው ሊንክ ያንብቡት! ሀሳብዎትን በአስተያየት መስጫው ላይ ያስቀምጡ !! Wondemsew Mesafint Kebadie Amanuel Zegeye Alelign D. Adane Abraham Shiferaw Kume sis abe Mastewal Addisu Yihunlamlak Wube Addisu Melkamu Hunegnaw Belete Addis Yeabsira Mekasha #እግርኳስ #ሻምፒዮንስሊግ2026 #ስፖርትሳይንስ #FootballAnalytics #SportsScience #TacticalAnalysis #UCLFinal26 #LuisEnrique #Arteta #PSG #Arsenal #PerformanceScience

Post content