Post by Birlew Animut
Sales & Marketing Coordinator at EVE sanitary production china campaign
#ስራ_ፍለጋ ትዕግስትና ጊዜ ይጠይቃል! 💼✨ ለእኛ ለአዲስ ተመራቂዎች (Fresh Graduates) ትልቁ ፈተና የሚጀምረው ከምረቃ ማግስት ነው። ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች "በእነዚህ በሶስት ሳምንት ውስጥ ስራ አጣን" ብለው በተስፋ መቁረጥ የሚያማርሩ ጓደኞቻችንን በተደጋጋሚ እያየን ነው። ነገር ግን እውነታውን እንጋፈጠው፡ አንድ ተቋም ማስታወቂያ አውጥቶ፣ ሲቪ (CV) መዝግቦ፣ አበጥሮ፣ ለፈተና እና ለቃለ-መጠይቅ (Interview) እስኪጠራ ድረስ ራሱ ቢያንስ ከአንድ ወር በላይ ሊፈጅ ይችላል። ይህ የቅጥር ሂደት (Recruitment Process) የራሱ የሆነ ጊዜ አለው። ስለዚህ መልእክቴ ግልጽ ነው፡ #እንታገስ፣ ታገሱ፡ ስራ ፍለጋ ራሱ የሙሉ ቀን ስራ መሆኑን አምነን በትዕግስት እንጠብቅ። #ስራ አንምረጥ፡ "ይህ ስራ ከእኔ ደረጃ ጋር አይመጥንም" ሳንል፣ እስከዛው ያገኘነውን በመስራት የስራ አለምን ልምድ እንቅሰም። ማንኛውም ትንሽ ጅማሮ ለትልቅ ስኬት በር ይከፍታል።