Post by Bereket Estifanos Haile
Chief Accountant at YMCA Ethiopia BA, MBA- Student , TAX ACCOUNTANT, FINANCIAL ACCOUNTANT, MANAGERIAL ACCOUNTANT
የዶ/ር የሮም ተማፅኖ!😭 "ልጄ ፀጋዘአብን አድኑልኝ" "እኔ ዶ/ር የሮም ጌታቸው እባላለሁ።ህመምተኞችን የመርዳት እና የህይወት ተስፋ የመስጠት ሙያ ውስጥ ብኖርም፣ የገዛ ልጄ ፀጋዘአብ "Ewing's Sarcoma" በተባለ አደገኛ የአጥንት ካንሰር ሲሰቃይ መመልከት ግን አቅም አሳጥቶኛል። የ3 ዓመት ከ6 ወር ህፃን፣ ገና መኖር ያልጀመረ ህይወት፣ በካንሰር ህመም ምክንያት ከበሬ ቆሞ እርዳታን ይጠይቃል። እስካሁን ያደረግነው የኬሞቴራፒ ህክምና በሽታውን ሊገታው አልቻለም። ሀኪሞቹ የልጄን ህይወት ለመታደግ በአስቸኳይ ወደ ውጭ ሀገር ተወስዶ የቀዶ ጥገና ህክምና እንዲያገኝ ወስነዋል። ነገር ግን ለዚህ ህክምና የሚጠየቀው 3.5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር የኔን የህይወት ዘመን ጉልበት እና አቅም የሚበልጥ ነው። ለልጄ ህይወት መታደግ ዛሬ የእናንተ የደጋግ ኢትዮጵያውያን እጅ ያስፈልገኛል። የኔ የህክምና እውቀት ዛሬ ለልጄ ምንም ሊፈይድለት አልቻለም፤ የእናንተ ግን የልጄን ህይወት ሊታደግ ይችላል። በአንድ አባት እሮሮ እማፀናችኋለሁ፤ ፀጋዘአብን ህይወት ለመታደግ የምትችሉትን ያህል ተባበሩኝ። ትንሹ ፀጋዘአብ በፈገግታ እንዲያድግ፣ እናንተ የህይወት ምክንያት ሁኑት። ለልግስናዎ የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ። Yerom Getachew Bekele CBE - 1000149557982 Abay Bank - 2091011011819814 Awash Bank - 013201344371300 Tele Birr: +251910119336 በጎ ፈንድ ሚ 👉 https://lnkd.in/dtagmE-F" ------- የእኔ፣ የጥላሁን ግርማ ማስታወሻና ተማጽኖ፣ ሊንክዲን ከተወሰነ በላይ connection ያላቸው ሰዎች ገንዘብ ካልከፈሉ በቀር ሌሎች ሰዎችን Tag እንዲያደርጉ የማይፈቅድ በመሆኑ ምክንያት ዶ/ር የሮምን tag ለማድረግ አልቻልኩም። ይሁንና በሚከተለው ሊንክ እንድታገኙት፣ እንድትወዳጁትና እንድታበረቱት አደራ እላለሁ።👇 https://lnkd.in/didtuZmW የሊንክዲን ወዳጆቼ ይሄንን ዜና ለሌሎች በማጋራት እንዲሁን የአቅማችሁን በማዋጣት ልጃችንን፣ ፀጋ-ዘአብን እንድናሳክም በቸሩ እግዚአብሔር ስም ጥሪዬን አስተላልፋለሁ። እንደማታሳፍሩኝ አውቃለሁ፣ አመሰግናለሁ!