Post by BELETE BANTERO, MA, MSc, PMP®, CIPM®, PhD Candidate
Global Business Development Partner for 365mesh-North America and Africa; BESS | Biz Dev Consultant | MA, MSc, PMP®, CIPM®, PhD Candidate | 28K+ Followers | Impact-Driven Leader
ከናዚም የከፋ ግፍ by Araya Tesfamariam አሸባሪው ሕወሓት በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች ከጦርነቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና ተቋማትን፣ ሙዚዬሞችን፣ መካነ ቅርሶችን እና የሐይማኖት ተቋማትን አውድሟል፡፡ እንደዚህ አይነት አውዳዊ ጦርነት ስልት እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1977 በወጣው የጄኔቫ ኮንቬንሽን አንቀጽ 54 ላይ የተከለከለ የጦርነት አካሄድ (ስልት) በሚል ተፈርጇል፡፡ የአሸባሪው ቡድን አባላት በሰሜን ሸዋ ዞን ዓለም በቃኝ ብለው ስጋቸውን የከዱ የ85 ዓመት መነኩሴን አስገድደው በመድፈር ናዚንም ይሁን አይኤስ አይኤስ የሽብር ቡድንን ያስናቀ ተግባር ፈፅመዋል፡፡ ወደ ሆስፒታል በመግባት ከበሽተኞች ላይ ኦክስጅን እና ጉሉኮስ በመንቀል በነብስ ውጪ ነብስ ግቢ ላይ ለነበሩ በሽተኞች እንኳን ቅንጣት ያክል ርህራሄ እንደሌላቸውም አሳይተውናል፡፡ ሽብርተኛው ሕወሓት በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች ከናዚም የከፋ ግፍ ፈጽሟል፡፡ የናዚው መሪ አዶልፍ ሂትለር በእብሪት እና ዘረኝነት ተነሳስቶ ከፋሽስት ጋር በመሆን መላውን አውሮፓ ለመውረር ጦር አዘመተ፡፡ የናዚ ጦር ወረራ ጅምሩ እጅግ የተሳካ ነበር፡፡ የጀርመን ጦር በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ የአውሮፓ ታላላቅ አገራትን መቆጣጠር ችሎ ነበር፡፡ ጦሩ ኖርዌን በሁለት ወር፣ ፖላንድን በአንድ ወር መቆጣጠር ሲችል ታላቋን ፈረንሳይ በስድስት ወር ውስጥ መሉ ለሙሉ በመቆጣጠር ወደ ምስራቅ አውሮፓ ግስጋሴውን ቀጥሎ የምስራቅ አውሮፓዎቹን ዩክሬን እና ቤላሩስን በመያዝ የመጨረሻ ግቡ ሞስኮ ሆነ፡፡ የናዚ ጀርመን ጦር ዋና ከተማዋን ሞስኮን አልሞ የሚያደርገውን ግስጋሴ ቀጥሎ ለሞስኮ መንደርደሪያ ይሆነው ዘንድ የኢንዱስትሪ ከተማዋን ስታሌንጋርድን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ዝግጅት አድርጎ 300 ሺሕ ሰራዊት አሰልፎ ወደፊት መግፋቱን ተያያዘው፡፡ ያኔ ሩሲያዊያን አባቶች አገራቸውን ከወራሪው ለማዳን ለመሞት ወስነው በፅናት በመቆም የናዚን ጦር በከበባ ውስጥ በማስገባት የመጀመሪያውን የሽንፈት ፅዋ አስጎነጩት፡፡ የስታሊንጋርድ ጦርነት የአሁኑን የዓለም ቅርፅ የቀየረ፣ አውሮፓን ከጀርመኑ ናዚ ወረራ የታደገ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት አሸናፊነትን የወሰነ የጦር ግንባር ነው፡፡ የአውሮፓን ግማሽ በቁጥጥሩ ስር አውሎ የነበረው የናዚ ጦር በሩሲያ ቀዩ ጦር የደረሰበትን ሽንፈት ተከትሎ ወደ ኋላ ለማፈግፈግ ተገደደ፡፡ ማፈግፈጉም ከሞስኮ አፍንጫ ስር እስከ በርሊን የዘለቀ ነበር፡፡ የናዚው ጦር በዚህ ማፈግፈግ ውስጥ አንድ አውዳሚ የሆነ የጦር ስልትን ተከተለ፡፡ ይህ ስልት ጠላት ሊጠቀምበት ይችላል ተብሎ የታመነበትን ሁሉንም ሀብት ማውደም "scorch earth policy" ሲሆን በዚህ አካሄድ ጠላት ሊጠቀምበት የሚችለውን ምግብ፣ መገናኛ እና ስነ-ተግባቦት መዋቅሮች፣ የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች እንዲሁም ኢንዱስትሪዎችን ማውደም ሲሆን ከፍ ሲልም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ለአቅመ ውትድርና የደረሱ ወጣቶችንም መጨፍጨፍ ይጨምራል፡፡ በዚህ አውዳሚ በሆነ የጦር እስትራቴጂ ዓለም አይታም ሰምታም የማታውቀውን ውድመት አስተናገደች፡፡ የናዚ ጦር ከሩሲያ ተነስቶ ወደ ዩክሬን ባደረገው ማፈግፈግ ብቻ 28 ሺሕ መንደሮች እና ከተሞችን አውድሟል፡፡ የጀርመኑ አዶልፍ ሂትለር የተጠቀመው ለጠላት ያገለግላሉ ያላቸውን ንብረቶች የማውደም ተግባር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከፍተኛ ውድመት በማስከተሉ እንዲህ አይነት ውድመት በዓለም ላይ ዳግም እንዳይደገም እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1977 በወጣው የጄኔቫ ኮንቬንሽን አንቀጽ 54 ላይ የተከለከለ የጦርነት ስልት በሚል ተፈርጇል፡፡