Post by Bank of Abyssinia
71,918 followers
ተጠንቅቀው ይገበያዩ! እንኳን ለትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! በበዓል ወቅት ግብይት ሲጨምር፣ አጭበርባሪዎችም በተለያዩ መንገዶች ደንበኞችን ለማጭበርበር ይሞክራሉ። ለምሳሌ በስልክ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ወይም በሀሰተኛ ድረ ገጾች … ወዘተ። የአቢሲንያ ባንክ አገልግሎቶችም በጠንካራ ደህንነት የታገዙ ቢሆኑም፣ እርስዎም የራስዎን ጥንቃቄ መውሰድ ይኖርብዎታል። እነዚህንም ጥንቃቄዎች ያድርጉ ፡- • ከመክፈልዎ በፊት የተቀባዩን መረጃ ያረጋግጡ • ግብይትዎን ያለ ችኮላ ያከናውኑ • ማንኛውንም ኮድ (OTP/PIN) ለሌሎች አያጋሩ • ያልተረጋገጡ ድረ ገጾች ላይ የካርድ መረጃዎን አያስገቡ • “ሽልማት አሸንፈዋል!” ብለው ገንዘብ የሚጠይቁ መልዕክቶችን አይመኑ • የባንኩን የተረጋገጡ የመረጃ ምንጮች ብቻ ይጠቀሙ አጠራጣሪ መልዕክት ካጋጠመዎ፣ በ8397 ይደውሉ ወይም ባቅራቢያዎ ለሚገኝ ቅርንጫፍ ያሳውቁ። መልካም የትንሣኤ በዓል! አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!