Post by Bank of Abyssinia
71,940 followers
ባንካችን የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተቸገሩ ወገኖች የአስቤዛ ድጋፍ አደረገ ! ባንካችን አቢሲንያ የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ሚያዚያ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ለተቸገሩ ወገኖች በዓይነት የ 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ። ድጋፉ የተደረገው በለሚ ኩራ፣በልደታ፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተሞችና በቢሾፍቱ ለሚገኙ ወገኖቻችን ነው። ይህን የበዓል መዋያ የአስቤዛ ድጋፍ ለገሀር በሚገኘው በትንሷ ስታዲየም በቦክስ ሜዳ የተደረገ ሲሆን የባንካችን ዴፒዩቲ ቺፍ ከስተመር ሪሌሽንሺፕና አክዊዜሽን ኦፊሰር የሆኑት አቶ ወሰንየለህ አበራ በዕለቱ ተገኝተው አስረክበዋል። በተጨማሪም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 7 ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ ነኢማ ሎባ በዕለቱ በመገኘት አቢሲንያ ባንክ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖቻችን በየጊዜው የሚያደርገውን ድጋፍ በማበረታታት በወረዳው ስም አመስግነዋል፡፡ በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ያሉ የህብረተሰባችንን ክፍሎች በመደገፍ ማህበራዊ ሃላፊነትን መወጣት የባንካችን አቢሲንያ ዋነኛ መገለጫ እና ቁልፍ ተቋማዊ እሴት እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን በዕለቱ የባንካችን የስራ ሃላፊዎች፤ በቂርቆስ ክ/ከ የወረዳ 7 የስራ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡