Post by Amhara Bank

23,389 followers

አማራ ባንክ፦ በወጀብ ውስጥ በፅናት እያለፈ፣ በህዝብ እምነት እየተገነባ የእድገት ጉዞውን በጥንካሬ ይቀጥላል። አዲስ አበባ አማራ ባንክ በይፋ ከተመሰረተበት ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በመቶ ሺዎች በሚቆጠሩ ባለአክሲዮኖች እምነት፣ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ደንበኞች ድጋፍ፣ በሰራተኞቹ ቁርጠኝነት እና በአገራችን ህዝብ በተሰጠው ከፍተኛ ተስፋ ላይ ተመስርቶ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ አንዱ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተቋም ሆኖ መገንባቱን ቀጥሏል። የባንካችን እድገት የአንድ ግለሰብ፣ የአንድ ቡድን ወይም የአንድ ውሳኔ ውጤት ብቻ ሳይሆን፣ በከፍተኛ ህዝባዊ ተሳትፎ እና ትብብር፡ በጋራ ኃላፊነት እና በጠንካራ ተቋማዊ መሠረት የተገነባ በፋይናንስ ዘርፍ በአገር-አቀፍ ብሎም በአለምአቀፍ ብቁ ተወዳዳሪ እና ብራንድ የመሆን ራዕይን ሰንቆ የተመሰረተ ባንክ ነው። አማራ ባንክ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት፡ የባለአክሲዮኖቹን እምነት፣ የደንበኞቹን ጥቅም እና የተቋሙን ተአማኒነት በማስጠበቅ የባንኩን ሥራ በሕግ፣ በሥርዓት እና በተቋማዊ መርሆዎች መሠረት ለማከናወን ቁርጠኛ መሆኑን ለሁሉም ባለደርሻ አካላት ማረጋገጥ ይወዳል። የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ራዕይ፡ ተልዕኮ እና ስትራቴጂ በውጤታማነት ሊመሩ የሚችሉ በባንክ ኢንዱስትሪው ውስጥ ከፍተኛ ልምድ እና እውቀት ያካበቱ የስራ ኃላፊዎችን መመሪያን እና ግልጽ መርህን በተከተለ እና በጠንካራ የውድድር ሂደት (Rigorous Competition Process) በመመልመልና ምርጫ በማካሄድ አደራጅቶ ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ላይ ይገኛል። ይሁን እንጅ ባንኩ ስራውን በተገቢው መንገድ እየሰራ ባለበት ሁኔታ በማህበራዊ ሚዲያ መሰረተ-ቢስ እና ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በባንኩ አመራር አባላት እና በባንኩ ደንበኞችም ጭምር የሀሰት መረጃ በማሰራጨት መልካም ስምን የሚያጎድፍ እና የባንኩን ገጽታ የሚያጠለሽ እኩይ ተግባር እየተፈፀመ በመሆኑ ባንኩ ለባለአክሲዮኖች፣ ለደንበኞች፣ ለተቆጣጣሪ አካላት፣ ለሰራተኞች እና ለመላው ህዝብ የሚከተለውን ማብራሪያ መስጠት ተገቢ፣ ትክክለኛና አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል። የአመራር ምልመላ ሂደት እና ተቋማዊ ግልጽነት ቦርዱ በማንኛውም የተቋም አስተዳደርና የአመራር ሂደት ውስጥ የሃሳብ ልዩነት መኖሩ ተፈጥሯዊ መሆኑን ያምናል። ሆኖም የሃሳብ ልዩነቶች የተቋሙን ህጋዊነት፣ የቦርዱን ስልጣን ወይም የባንኩን ተቋማዊ ጥንካሬ የሚያሳጡ እንዳልሆኑ ለህዝብ ማረጋገጥ ይወዳል። የባንኩ ከፍተኛ አመራር ምልመላና ምርጫ ሂደት በቦርዱ በፀደቁ የኮርፖሬት ገቨርናንስ መመሪያዎች፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተፈጻሚ በሆኑ መመሪያዎችና መስፈርቶች መሠረት ብሎም በተቋሙ የውስጥ አሠራር ስርዓቶች መሠረት ደረጃ በደረጃ ተከናውኗል። ሂደቱ በብቃት፣ በሙያዊ ብስለት፣ በተገቢ ምዘና እና የአመራር ብቃትን መሰረት ባደረጉ መስፈርቶች ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ በየደረጃው የተሰጡ ውሳኔዎችም በህጋዊና ተቋማዊ ሂደት ተመርተዋል። በሂደቱ ውስጥ፦ ሙሉ ዜናውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጠቀሙ። https://shorturl.at/Y4WCb አማራ ባንክ ከባንክ ባሻገር!

Post content