Post by Amanuel Girma

Founder & CEO at Halink Technology PLC | Full Stack Developer | AI & SaaS Builder

​ሁላችንም የAI (Artificial Intelligence) ውጤቶችን እንወዳለን፣ በስራችን ላይ የሚፈጥረውን ምቾት እና ለውጥ ማየት እንፈልጋለን። ነገር ግን "እንዴት ነው የሚሰራው? እኔስ እንዴት መገንባት ወይም በስራዬ ላይ ማዋል እችላለሁ?" ወደሚለው ተግባራዊ ጥያቄ ስንመጣ ግን ብዙዎቻችን እንቀዘቅዛለን። በተለይ ደግሞ እንደ Python ያሉ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎችን እና መሠረታዊ ነገሮችን መማር ሲነሳ ነገሩ አስፈሪ ሊሆን ይችላል። ​እውነታው ግን ይህ ነው፦ ያለ ጠንካራ መሠረት ትልቅ ህንፃ መገንባት አይቻልም። AI የዛሬም የነገም መፃኢ እድላችን ነው፤ እሱን በትክክል ተረድቶ ለመጠቀም ግን የጀርባ አጥንቱ የሆኑትን መሠረታዊ ነገሮች (Fundamentals) ማወቅ ግድ ይላል። Python ደግሞ ለዚህ ትልቁ እና ቀላሉ መግቢያ በር ነው። ​መጀመሪያ ላይ ኮዲንግ መማር ወይም አዲስ ቴክኖሎጂ ውስጥ መግባት ያስፈራ ይሆናል፣ ግን አንዴ መሠረቱን ከያዙት በኋላ የሚከፍተው የዕድል በር በጣም ሰፊ ነው። ቴክኖሎጂን ዝም ብሎ ከአድናቂነት እና ከተጠቃሚነት ባለፈ፣ ተረድቶ ወደ ፈጣሪነት ለመቀየር ይሄንን የመጀመሪያውን "የመፍራት" ስሜት ሰብሮ ማለፍ ያስፈልጋል። ​ከምኞት ባለፈ በተግባር መማር ሲጀመር ነው እውነተኛ ለውጥ የሚመጣው።

Post content