Post by Alazar Getachew

AP & AR Specialist at Soufflet Malt Ethiopia Sc

Part #3 አይደርስም አትበሉ! ​ትላንትና ስለ ታክስ አደጋ ስጋት Tax Risk ያጋራሁትን ፅሁፍ አይቶ አንድ ወዳጄ የደረሰበትን እውነተኛ ታሪክ ያጫወተኝ ላጋራችሁ። ወሬውን ከሰማሁበት ሰዓት ጀምሮ በአምሮዬ የመጣው አንድ ነገር ብቻ ነው የታክስ ህጎችን ቸል ማለት እና አሰራርን አለማስተካከል ድርጅቶችን ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል ነው። ​ነገሩ እንዲህ ነው ወዳጄ የሚሰራበት ትልቅ ድርጅት ውስጥ ያጋጠመውን እና ድርጅቱን ከፍተኛ ዋጋ ያስከፈለውን አንድ ትልቅ የታክስ አደጋ ላጋራችሁና እናንተም ተማሩበት or ተጠንቀቁበት። ​የተበላሸ የዕቃ ክምችትን ከመዝገብ መሰረዝን Inventory Write-off በተመለከተ ነው። 🧱​በትላልቅ ድርጅቶች ውስጥ ጥሬ ዕቃዎች ወይም ምርቶች በብልሽት ፣ ጊዜያቸው በማለፉ Expiry ወይም በጥራት መጓደል ምክንያት ጥቅም ላይ ሊውሉ የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው የተለመደ ነው። በፋይናንስ መርህ መሠረት ደግሞ ይህንን ዕቃ ዋጋ የሌለው መሆኑን አረጋግጦ ከመዝገብ ላይ መቀነስ Write-off እና እንደ ወጪ መመዝገብ ግዴታ ነው ድርጅቱም ያደረገው ይሄንንኑ ነበር። 👉​ነገር ግን እዚህ ጋ ነው ዋናው ችግር የተፈጠረው ​የታክስ አደጋው እና የተሰራው ስህተት:- ​የታክስ ኦዲተሮች ድርጅቱን ኦዲት በሚያደርጉበት ጊዜ ይህንን የተሰረዘ ዕቃ ወጪ በቀላሉ እሺ ብለው አልተቀበሉትም🤔🤔 ✍️ኦዲተሮቹ ያነሱት ጥያቄ፦ 🙆‍♂️​ዕቃው መበላሸቱን በምን እናውቃለን ምናልባት በህገወጥ መንገድ ያለደረሰኝ ሸጣችሁትስ ቢሆንስ የሚል ጥርጣሬ ነበር። ​በታክስ ህጉ መሰረት የተበላሸ እቃ ከሂሳብ መዝገብ ላይ ሲቀነስ የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ነበረባቸው 🏖️ ​ለገቢዎች መስሪያ ቤት በደብዳቤ ማሳወቅ:-​የገቢዎች ታክስ ኦዲተር እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት እቃው እንዲወገድ Dispose ማድረግ እና ቃለ ጉባኤ መያዝ ነበረባቸው። ​ይህ አሰራር ባለመከናወኑ ምክንያት ኦዲተሮቹ ያንን የተበላሸ እቃ ወጪ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አደረጉት ​ ☠️የቸልተኝነት ውጤት ያደረሰው ጉዳት ​ይህ ወጪ ውድቅ ከተደረገ በኋላ ድርጅቱ ላይ የመጣው ኪሳራ ቀላል አልነበረም √.​የትርፍ ግብር Corporate Income Tax ድርጅቱ ባልሸጠው እና ገቢ ባላገኘበት ዕቃ ላይ የትርፍ ግብር እንዲከፍል ተገደደ። √.​ቀደም ሲል ያወራረደው ቫት Inout VAT ማለትም ዕቃው ሲገዛ የተወራረደውን ቫት Input VAT ለገቢዎች መልሱ ተባለ። ​ ብዙ ክምችት ላለው ትልቅ ኮርፖሬት ይህ ምን ያህል ከባድ አደጋ እና የገንዘብ ኪሳራ እንደሆነ መገመት ትችላላችሁ። 🫵​መልእክቴ እና ማሳሰቢያዬ ​ወዳጆቼ ታክስ ማለት ዝም ብሎ በየወሩ ሪፖርት ማድረግ ብቻ አይደለም። በየቀኑ የምናደርጋቸው የውስጥ አሰራሮች እና የምንወስናቸው ውሳኔዎች ሁሉ የራሳቸው የታክስ አንድምታ አላቸው። ​የእቃ ክምችት Inventory የምታስተዳድሩ ድርጅቶች ማንኛውንም እቃ ከመዝገብ ከመቀነሳችሁ በፊት ከታክስ አማካሪዎቻችሁ ወይም ከህጉ ጋር ማመሳከራችሁን እንዳትረሱ ​ዛሬ የምናሳየው ጥቃቅን ቸልተኝነት፣ ነገ ድርጅታችንን ሊያዘጋ የሚችል ትልቅ የታክስ እዳ ሆኖ ሊመጣ ይችላልና እንጠንቀቅ!!!። ​ 🫴ተመሳሳይም ሆነ የምታውቁት እና ከዚህ በፊት አጋጥሟችሁ የተማራችሁበት አጋጣሚዎች ካሉ ሰዎች ይማሩባቸው ዘንድ ሀሳቦቻችሁን ለማጋራት ንፋግ አትሁኑ። 🤝በመጨረሻም አሁን እንዴት ነው ህጎችን የመከታተለ እና ከገቢዎች ጋር ያለህ ግንኙነት ብዬ ላነሳሁለት ጥያቄ የሰጠኝ ፈገግ የሚያሰኝ መልስ ይህ ነበር:- "እንኳን የነበሩትን ይቅርና አዳዲስ ህጎችን እግርበግር እየተከታተልኩ የቄሳርን ለቄሳር (ቄሳር ያው ባለሀብቱ ነው😆) የገቢዎችን ለገቢዎች ነው ብሎኝ እርፍ'' A.G👍